እንኳን ወደ ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በደህና መጡ!

መለያችን ደራሽነታችን!!

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርትድርጅት

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስና የሰብአዊ ድጋፍ ታሪክ ውስጥ የማይጠፋ ዘላቂ አሻራ ያሳረፈ፣ በአስተማማኝነቱና በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቅ አንጋፋ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው። ይህ ተቋም በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተው በመንግስት ልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት በጥቅምት 20 ቀን 1990 ዓ.ም. በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 21/1997 ነበር።

ERTE Gate

+

የተሽከርካሪ ብዛት

+

በስራው ላይ ያለን ልምድ

+

የተሰጡ አገልግሎቶች

+

ደንበኞቻችን

ወ/ሮ ኤደን ግርማ

የዋና ስራ አስፈጻሚው መልዕክት

ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የጭነት ትራንስፖርት ታሪክ ውስጥ የማይጠፋ ዘላቂ አሻራ ያሳረፈ፣ በአስተማማኝነቱና በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቅ አንጋፋ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን፤ ስትራቴጂካዊ ተልዕኮውንም በሁለት አበይት ምሶሶዎች ላይ መስርቶ ይንቀሳቀሳል። በአንድ በኩል፣ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለሚከሰቱ አደጋዎች ፈጣንና ቀልጣፋ የድንገተኛ እርዳታ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሕብረተሰቡ በማድረስ የዜጎችን ሕይወት የመታደግ አጣዳፊ አገራዊ ኃላፊነቱን በቁርጠኝነት የሚወጣ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ የአገሪቱን የንግድ ፍሰትና የኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የጭነት ትራንስፖርት አቅሙን በማሳደግና አስተማማኝ የሎጂስቲክስ ሰንሰለት በመዘርጋት ለንግዱ ማኅበረሰብና ለሀገር ዕድገት የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ከተቀመጡት ዋና ዋና ዓላማዎች በተጨማሪ ድርጅቱ ለረጅም ዓመታት ባካበተው ሰፊ ልምድ ለበርካታ የመንግሥትና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ደረጃውን የጠበቀ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬቱ ደግሞ አስተማማኝ ሰላም፣ የተሟላ የተሽከርካሪዎች ስምሪት ዝግጁነት፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል እና ዘመናዊ አሰራርን በአግባቡ መጠቀም መቻሉ ቁልፍ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮለታል።

CEO

ወ/ሮ ኤደን ግርማ

ዋና ስራ አስፈጻሚ

የድርጅቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች

የድርጅታችን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች ለዘላቂ እድገትና ለላቀ አገልግሎት መሠረት ናቸው።

Vision

ራዕይ

"በ2020 በኢትዮጵያ ተመራጭና ተወዳዳሪ የዕርዳታና የንግድ ጭነት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሆኖ መገኘት"

Mission

ተልዕኮ

የዕርዳታ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት፤ ማንኛውንም የንግድና የልማት ጭነት አገልግሎት መስጠት፤ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት መስጠት፣ ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚያግዙ ሌሎች ተዛማጅ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን ማከናወን።

Values

እሴቶች

✓

ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንሰጣለን።

★

የድርጅቱን መልካም ስምና ዝናን ጠብቀን እናቆያለን።

⚡

ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን።

💡

ሀብትን በቁጠባ በመጠቀም ለወጪ ቅነሳ ልዩ ትኩረት እንሰጣለን።

❤️

የውጤታማነታችን መለኪያ የደንበኞቻችን እርካታ ነው።

🛡️

የሠራተኞቻችንን ጤንነት ከበሽታ መከላከል የሥራችን አካል ነው።

🤝

ለሕሊናችን እና ለማህበረሰባችን ታምነን እንሠራለን።

አገልግሎቶቻችን

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ድርጅታችን በከፍተኛ ጥራት፣ በፍጥነት እና በአስተማማኝነት የተለያዩ የትራንስፖርትና የጥገና አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የዕርዳታ እህልና ቁሳቁስ ማጓጓዝ

የዕርዳታ እህልና ቁሳቁስ ማጓጓዝ

የዕርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ማዕከላዊ መጋዝኖች ወደ ተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በፍጥነት እና በደህንነት የማጓጓዝ አገልግሎት እንሰጣለን።

የንግድ ጭነቶችን ማጓጓዝ

የንግድ ጭነቶችን ማጓጓዝ

የማንኛውንም የንግድ ጭነቶችን በአገር ውስጥ እና ከወደብ ወደ አገር ውስጥ በዘመናዊ የሎጂስቲክስ ስርዓት በመጠቀም በአስተማማኝ ሁኔታ እናጓጉዛለን።

የተሽከርካሪ ጥገና

የተሽከርካሪ ጥገና

ለከባድ፣ ለመካከለኛ እና ለቀላል ተሸከርካሪዎች የሜካኒካል፣ የኤሌክትሪክ እና የቦዲ ጥገና አገልግሎት በብቁ ባለሙያዎች እንሰጣለን።

የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች

ትራከር

ትራከር

የአንዱ የመጫን አቅም: 400 ኩንታል

ብዛት: 70

ሬኖልት

ሬኖልት

የአንዱ የመጫን አቅም: 510 ኩንታል

ብዛት: 15

ሲኖ ትራክ

ሲኖ ትራክ

የአንዱ የመጫን አቅም: 400 ኩንታል

ብዛት: 100

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

የቅርብ ጊዜ ዜናዎቻችንን፣ የድርጅት ዝማኔዎችን፣ የሥራ ስኬቶችን እና አስፈላጊ ማስታወቂያዎችን ይመልከቱ።

ሁሉንም ዜናዎች ለመመልከት→
የምስክር ወረቀት

የምስክር ወረቀት እና እውቅናዎች

ዕለት ደራሽ የሙያ ደረጃዎችን ይጠብቃል እንዲሁም ከአገር አቀፍ እና ከአለም አቀፍ የትራንስፖርት፣ የሎጂስቲክስ፣ የደህንነት እና የጥራት አስተዳደር መስፈርቶች ጋር ይጣጣማል።

እስካሁን የተመዘገበ የምስክር ወረቀት የለም።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና ማስተባበሪያ ጣቢያዎች

የድርጅቱ ዋና መ/ቤት በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሲሆን፣ በኮምቦልቻ፣ ያቤሎ እና አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም አሉ።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

አዳማ

አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ጅቡቲ

ጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ጣቢያ

ኮምቦልቻ

ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጣቢያ

ጣቢያ

ድሬዳዋ

ድሬዳዋ ማስተባበሪያ ጣቢያ

ጣቢያ

ያቤሎ

ያቤሎ ማስተባበሪያ ጣቢያ

ጣቢያ

ሚሌ

ሚሌ ማስተባበሪያ ጣቢያ

የጭነት አገልግሎት ዋና ዋና ደንበኞች

በሕዝብ እና በግል ዘርፍ አጋሮች የምንታመን ነን - ከታች ያሉት አርማዎች ተወካይ ናቸው።

የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ዋና ዋና ደንበኞች

በሕዝብ እና በግል ዘርፍ አጋሮች የምንታመን ነን - ከታች ያሉት አርማዎች ተወካይ ናቸው።